ያኔ በልጅነት ከማሳው ወሰድኸኝ፣

አፈሩን ጨብጠህ እስኪ አሽትተው አልኸኝ።

የድንጋዮቹ ስም የምንጮቹ ታሪክ፣

የአዝርዕቶቹ አይነት የአበባወቹ መልክ፣

የእንስሳቱ ጸባይ የመሬታችን ልክ፤

ተራራው ገላ ላይ የጥንት ኮቴወች፣

አዝመራና መንገድ እርሻና ጎጆወች፤

ከመንደሩ መሃል ቅዱሳን አጸዶች::

መሬቱን በቃልህ ጠቀለልከውና፣

ልቤ ጋር አሠርኸው በቀስተ ደመና።

 

ከዚያን ጊዜ ወዲህ፦

አፈርን  እንደአካል ዘርን እንደነፍስ፣

ተራራን እንደህልም ዛፍን እንደልብስ፤

አዝርዕቱን እንደህዝብ ልቤ ላይ ከትሜ፣

ስኖር አይደክመኝም ሃገር ተሸክሜ።

 

English

During childhood you took me to the field

you held the soil and asked me to smell it

the names of stones, the stories of rivers

the varieties of seeds, the colours of flowers

the character of animals, the reach of our land

ancient footprints on the body of mountains

crops and roots, farms and huts

sacred trees at the centre of our village.

You wrapped the land with your words

and tied it to my heart with green, yellow

and red.

 

Since that time

flesh like soil, soul like seeds

dreams like mountains, cloth like trees

people I gather in my heart like crops.

I do not feel tired when I live carrying a country.